top of page

የመፅሀፉ ይዘት የሚያተኩረው ያለፍኩባቸውን፤ የተሳተፍኩባቸውን እና የታዘብኳቸውን የግል ትውስታዎች ነው። "ትውስታዎቼ " በአፄው ዘመን የነበረውን የመሬት ሥሪት ከዳሰሰ በኋላ ሥሪቱን ለማስተካከል የተሞከሩና ሳይሳኩ የቀሩ ጥረቶችን ካስታወሰ በኋላ አዋጅ አወጣጥና አፈፃፀም በዝርዝር ያስረዳል።  ቀጥሎም  የደርግን አገዛዝ ለመጣል ኢህአፓ ባደረገው የትጥቅ ትግል የነበረኝን ተሳትፎና አሜሪካ ከገባሁ በኋላም የኢትዮጱያ ዴሞክራሲያዊ ህብረት ቅንጀትን በመወከል በአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ በካርተር ማዕከልና በነጩ ቤተ መንግሥት የነበረኝን ተሳትፎና የታዘብኳቸውን ኩነቶች አካቷል። ከዚያም ወያኔ የቤጌምድርና ስሜን ክፍለሀገርን ህዝብ በጎሣ ለመከፋፈል የወጠነውን  ዕቅድ ለማክሸፍ በውጭ ሀገር የሚኖሩ የክፍለሀገሩ ተወላጆች ባድረጉት እንቅስቃሴ የነብረኝን ተሳትፎ ያትታል። በመጨረሻም  ኢትዮጵያንና ሱዳንን ለዘመናት ሲያወዛግብ ስለቆየው የድንበር ጥያቄ ከእንግሊዝ ሀገር መዛግብት ያገኘኋቸውን መረጃዎች ዋቢ በማድረግ የድንበሩ ጉዳይ የሱዳን መንግሥት እንደሚለው እንዳልሆነ ለማሳዬት ሞክሯል።

’እጅጉን ያስቸግር የነበረው የመሬት ይዞታን ለማሻሻል ቀደም ባሉት ዓመታት ይካሄዱ በነበሩ ጥናቶች ውስጥ በመሳተፍ፤ ከ1966 ዓ ም አብዮት በኋላ ደግሞ የወጣውን አዋጅ በማርቀቅና ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ወሳኝ አስተዋጽኦ ካበረከቱት ሠራተኞች መካክል አንዱ ይህ ደራሲ ነበር። ይህ ጉዳይ ብዙ ያከራከረ፣ ያፋጀ፣ የወዳጅ መንግሥታትን ትኩረትም የሳበ ነበር። በዚህ ዙርያ የተከሰተውን ሁሉ በቅጡ አስተውሎ ሐቀኛ የታሪክ ምሑራን በሚፈልጉት ዓይነት መመዝገብ ቀላል አይደለም። ከዚህ አንጻር ደራሲው ሃላፊነቱን በሚገባ በዚህ መጽሐፈ ተውጥቷል ለማለት እንችላለን።”                                                             

  —ተካልኝ ገዳሙ

ትውስታዎቼ: ስለመሬት ይዞታና የተለያዩ ፓለቲካዊና አገራዊ ጉዳዮች

SKU: 9781569028834
$24.95Price
Quantity
  • ዓለምአንተ ገብረሥላሴ

No Reviews YetShare your thoughts. Be the first to leave a review.
Product Page: Stores_Product_Widget

(202) 234-4755 Store | (202) 588-7061 Cafe

2714 Georgia Ave NW, Washington, DC 20001, USA

©2024 Sankofa Video Books & Cafe

Web Design and Photography of Sankofa by melkETsadek

  • facebook
  • googlePlaces
  • twitter
  • instagram
  • googlePlus
bottom of page